ይህ ገጽ ከታዋቂ ሰዎች: ከስነ ጽሁፍ ስራዎችና ሌሎች የፈጠራ ስራዎች የሚጠቀሱ ሰነዶችንና የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎችና ከሌላም ቋንቋ የተተረጎሙ ጥቅሶችን ለማሰባሰብና ለማስተዋወቅ የቀረበ ነው:
የታዋቂ ሰዎች ጥቅሶች
"የሚያስፈልገው ግንዛቤ፣ ሃይል ያለ ፍቅር ሃላፊነት-አልባና ግፈኛ፣ ፍቅር ያለ ሃይል ደግሞ ስሜታዊና ልፍስፍስ መሆኑ ነው፡፡ ሃይል ድንቅ የሚሆነው ፍቅር የፍትህን ጥያቄ ሲመልስ ነው፤ ፍትህ ድንቅ የሚሆነው ደግሞ ሃይል የፍቅር እንቅፋትን የሚያነሳ ሲያስተካከል ነው...። ለሰው ልጅ ችግር መልስ የሚሰጠው ፍቅር መሆኑን አውቃልሁ፣ እኔም በሄድኩበት ሁሉ ስለሱ ልናገር ነው።" ~ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጅንየር
"What is needed is a realization that power without love is reckless and abusive, and love without power is sentimental and anemic. Power at its best is love implementing the demands of justice, and justice at its best is power correcting everything that stands against love... I know that love is ultimately the only answer to mankind's problems. And I'm going to talk about it everywhere I go." ~ Martin Luther King, Jr.
«አንዳንድ ሰዎች የሕይወቴን ታሪክ ጽፈው ባለማወቅ ወይም በመሳሳት ወይም በምቀኝነት ዕውነትን አስመስለው ለሌሎች እንዲመስል ቢሞክሩም የዕውነተኛውን ነገር ከሥፍራው ሊያናውጡት አይችሉም።» ~ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
«Some people have written the story of my life representing as truth what in fact derives from ignorance, error or envy; but they cannot shake the truth from its place, even if they attempt to make others believe it.» [Haile Sellasie]
«ቋንቋ የምናስበውን ፈይዶ ይቀርፃል፣ እናም ልናስብ የምንችለውን ገደብ በይኖ ይወስናል።» ቤንጃሚን ሊ ዎርፍ
“Language shapes the way we think, and determines what we can think about.” Benjamin Lee Whorf
«....ማንም ሰው ለመማርና ለመሠልጠን መድከም አለበት።» ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በ፲፰፻፺፰ ዓ.ም ስለትምሕርት ያስነገሩት አዋጅ
«እናንተ አንድ ልብ ከሆናችሁ በምቀኝነት እርስ በርሳችሁ ተዋግታችሁ ካላለቃችሁ በቀር ኢትዮጵያን አገራችንን ለሌላ ለባእድ አትሰጧትም፤ ክፉም ነገር አገራችንን አያገኛትም። ነፋስ እንዳይገባባችሁ አገራችሁን በያላችሁበት በርትታችሁ ጠብቁ፤ ወንድሜ ወንድሜ እየተባባላችሁ ተደጋገፉ፤ የኢትዮጵያን ጠላት ተጋግዛችሁ ተደንበር መልሱ። የኢትዮጵያ ጠላት ባንዱ ወገን ትቶ ባንድ ወገን ቢሄድና ደንበር ቢገፋ፤ በኔ ወገን ታልመጣ ምን ቸገረኝ ብላችሁ ዝም አትበሉ፤ ያ ጠላት በመጣበት በኩል ኁላችሁም ሄዳችሁ አንድነት ተጋግዛችሁ ጠላታችሁን መልሱ እስከ እየቤታችሁ እስኪመጣ ዝም ብላችሁ አትቆዩ»
ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ፤ግንቦት ፲ ቀን ፲፱፻፩ ዓ.ም.
«በአንድ በኵል፣ ሁሉ የመግባቢያ ዘይቤ ዓይነት፣ በግለሰብ ላይ ተፅእኖ የሚያውለው፣ ከማኅበረሰባዊ መንስዔዎች በመመንጨት ነው፣ በተለይ
ከግልሰቡ አፍ መፍቻ ቋንቋው።» ኤድዋርድ ሳፒር
«In a sense, every form of expression is imposed upon one by social factors, one's own language above all.» Edward Sapir
"በሥራህ ላይ ሳይሆን በራስህ ላይ እንዴት ጠንክረህ መሥራት እንዳለብህ ተማር። ሥራህ ላይ ጠንክረህ ከሠራህ የእለት ጉርስህን ታገኛለህ፤ በራስህ ላይ ጠንክረህ ከሠራህ ግና ባለ ፀጋ ትሆናለህ!" ጅም ሮን
Learn to work harder on yourself than you do on your job. If you work hard on your job you’ll make a living, if you work hard on yourself you can make a fortune."
|